ጥ4: አንዳንድ መሸጥ የተከለከሉ የግብይት ዓይነቶችን ጥቀሱ?

መልስ-

1- ማጭበርበር: ለምሳሌ የሸቀጥን ነውር መደበቅ፤

የማጭበርበር ክልከልነትን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በአንድ የእህል ክምር -ማለትም የምግብ ክምር- በኩል እያለፉ ሳሉ እጃቸውን ወደ እህሉ ከተቱና ጣቶቻቸው አንዳች እርጥበት ሲያገኘው እንዲህ አሉ፡- “የእህሉ ባለቤት ሆይ! ይህ ምንድን ነው ይሄ?” እርሱም፡- "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ዝናብ መትቶት እኮ ነው" አላቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉት፦ "(የእርጥብ ክፍሉን) ሰዎች እንዲያዩት ከክምሩ በላይ በኩል ለምን አላስቀመጥከውም? የሚያጭበረብር ከኛ አይደለም።" ሙስሊም ዘግበውታል።

2- አራጣ፡- ለምሳሌ ከሆነ ሰው አንድ ሺህ ተቀብሎ ሲመልስለት ግን ሁለት ሺህ አድርጎ መመለስ ነው።

በእዳው ላይ የተጣለው ጭማሪ አራጣ ነው።

የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {መሸጥን አላህ ፈቅዷል። አራጣንም እርም አድርጓል።} [ሱረቱል በቀራህ 275]

3- አልገረር ወ አልጀሃላህ፡- ይህ ሲባል በበግ (በፍየል) ጡት ውስጥ ያለን ወተት አልያም ሳይታደን በባህር ውስጥ ያለን አሳ መሸጥ የመሳሰሉትን የሚያካትት ነው።

በሐዲሥ እንደመጣው፡ (የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "የገረር" ሽያጭን ከልክለዋል።) ሙስሊም ዘግበውታል።