1- በክፋት የምታዝ ነፍስ፡- ይህም የላቀው አላህን በማመፅ በኩል የሰው ልጅ ነፍሱንና ስሜቱ ያዘዘችውን ነገር መከተሉ ነው። ጥራት ይገባውና፡ {ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና። ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» (አለ)።} [ሱረቱ ዩሱፍ፡ 53] 2- ሸይጧን፡- የሰው ልጅን ማጥመምና በክፋት ወስውሶ እሳት የማስገባት ዓላማ ያለው የሰው ልጆች ጠላት ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡- {የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከታተሉ። እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና።} [ሱረቱል በቀራህ 168] 3- መጥፎ ጓደኞች፡- ክፋትን የሚያበረታቱና ከመልካም የሚከለክሉት ናቸው። አላህ እንዲህ ብሏል፡- {ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው። አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ።} [ሱረቱ ዙኽሩፍ፡ 67]