መልስ-1- አያተል-ኩርሲይ እቀራለሁ፡- "አልላሁ ላ ኢላሃ ኢላ ሁወል ሓዩል ቀዩም ላ ታእኹዙሁ ሲነቱን ወላ ነውም፤ ለሁ ማ ፊሰማዋቲ ወማ ፊል አርዲ፤ መንዘለዚ የሽፈዑ ዒንደሁ ኢላ ቢኢዝኒህ፤ ያዕለሙ ማ በይነ አይዲሂም ወማ ኸልፈሁም፤ ወላ ዩሒጡነ ቢሸይኢን ሚን ዒልሚሂ ኢላ ቢማ ሻአ፤ ወሲዐ ኩርሲዩሁ ሰማዋቲ ወልአርድ፤ ወላ የኡዱሁ ሒፍዙሁማ ወሁወል ዓሊዩል ዓዚም።" {አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ሕያው ራሱን ቻይ ነው። ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም። በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው። ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢሆን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል። በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)። መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ። ጥበቃቸውም አያቅተውም። እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው።} [ሱረቱል በቀራህ፡ 255] 2- እንደሚክተለውም (ሱረቱል ኢኽላስንና ሁለቱን ቁል አዑዙ) እቀራለሁ፡- በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። {በል «እርሱ አላህ አንድ ነው። (1) አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። (2) አልወለደም፤ አልተወለደምም። (3) ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም። (4)} ሦስት ጊዜ። በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። {በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ። (1) ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት። (2) ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ። (3) በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከሆኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት። (4) ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ፤ (እጠበቃለሁ በል)። (5)} ሦስት ጊዜ። በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። {በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ። (1) የሰዎች ሁሉ ንጉሥ በሆነው። (2) የሰዎች አምላክ በሆነው። (3) ብቅ እልም ባይ ከሆነው ጎትጓች (ሰይጣን) ክፋት። (4) ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከሆነው። (5) ከጋኔኖችም ከሰዎችም (ሰይጣናት እጠበቃለሁ በል)። (6)} ሦስት ጊዜ። "አላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ ወ አነ ዐላ አህዲከ ወዋዕዲከ መስተጣዕቱ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ሶናዕቱ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ ወአቡኡ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ ፈኢነሁ ላ የግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንት"
(ትርጉሙም፡ አላህ ሆይ አንተ ጌታዬ ነህ ከአንተ በቀርም አምልኮ የሚገባው የለም። አንተው ፈጠርከኝ እኔም ባሪያህ ነኝ። ቃል ኪዳንህንና ለአንተ የገባሁትንም ቃል ለመጠበቅ የቻልኩትን ያህል እጥራለሁ። በኔ ላይ ባለህ ችሮታና ኃጢአቴንም የማምን በመሆኔ ከሰራሁት ክፋት በአንተው እጠበቃለሁ። ማረኝ ከአንተ በቀር ኃጢአትን የሚምር የለምና።) ቡኻሪይ ዘግበውታል።