ጥ21፡ ከተከለከለው የማጭበርበር ዓይነት የተወሰኑትን ይጥቀሱ?

መልስ - በመግዛትና በመሸጥ ላይ ማጭበርበር፡ ይህም የሸቀጦችን እንከን በመደበቅ ሊሆን ይችላል፤

- በመማር ማስተማር ማጭበርበር፡ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ መኮረጃቸውን ይመስል፤

- በቃል ማጭበርበር፡ የውሸት ምስክርነትንና ውሸትን ይመስል፤

- ከሰዎች ጋር የተስማሙትን ቃል አለመሙላትን መጥቀስ ይቻላል።

የማጭበርበር ክልከልነትን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በአንድ የእህል ክምር በኩል እያለፉ ሳሉ እጃቸውን ወደ እህሉ አስገቡና ጣቶቻቸው አንዳች እርጥበት ሲያገኘው እንዲህ አሉ፡- “የእህሉ ባለቤት ሆይ! ይህ ምንድን ነው?” እርሱም፡- "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ዝናብ መትቶት እኮ ነው" አላቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉት፦ "(የእርጥብ ክፍሉን) ሰዎች እንዲያዩት ከክምሩ በላይ በኩል ለምን አላስቀመጥከውም? የሚያጭበረብር ከኛ አይደለም።" ሙስሊም ዘግበውታል።

በሐዲሡ "አስ-ሱብራ" የተባለው የእህል ክምሩ ነው።