ጥ 19፡ ትሕትናን ምን ማለት ነው?

መልስ - ትሕትና ማለት የሰው ልጅ ራሱን ከሌሎች የተሻለ አድርጎ ላያይ፤ ሰውንም ላይንቅና እውነታንም ላይገፈትር (ሊቀበል) ነው።

የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {የአርረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚሄዱት... ናቸው።} [ሱረቱል ፉርቃን፡ 63] ማለትም፡ ትሁት ሆነው። የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ማናችሁም ራሱን ለአላህ ብሎ ዝቅ ካደረገ አላህ ከፍ ያደርገዋል።" ሙስሊም ዘግበውታል። በሌላም ሐዲሥ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህም ብለዋል፦ “ማንም ሰው ሌላው ላይ ድንበር እስከማይተላለፍና አንዱ በሌላው ላይም እስከማይመፃደቅ ድረስ እርስ በርሳችሁ ትሑት ትሆኑ ዘንድ አላህ ወደኔ ወሕይ (መለኮታዊ ራእይ) አውርዶልኛል።" ሙስሊም ዘግበውታል።