ጥ16፡ ፈገግታ ምንድን ነው?

መልስ - ሰዎችን ሲያገኙ በፍካት ደስታንና አዛኝነትን ፊት ላይ አጉልቶ ማንፀባረቅ ነው።

ሰዎችን የሚያርቃቸው ከሆነው ፊትን የማኮሳተር ተቃራኒ ነው።

የፈገግታን የላቀ ደረጃ በተመለከተ ብዙ ሐዲሦች የመጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከአቡ ዘር (ረዲየላሁ ዐንሁ) በተላለፈ ሐዲሥ ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ እንዳሏቸው ገልፀዋል፡- "ወንድምህን በፈገግታ የተሞላ ፊት ማሳየትንም ቢሆን መልካም ነገርን እንደ ቀላል ነገር አድርገህ አትመልከት።" ሙስሊም ዘግበውታል። የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "በወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህም ምጽዋት ነው።" ቲርሚዚይ ዘግበውታል።