ጥ 15፡ የመዋደድ ባህርይ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?

መልስ - የላቀው አላህን መውደድ።

የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው።} [ሱረቱል በቀራህ 165]

የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንን መውደድ።

እንዲህ ብለዋል፦ "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ማናችሁም ዘንድ ከአባቱ፣ ከልጁና ከሰው ልጆች ሁሉ ለርሱ ይበልጥ ተወዳጁ እኔ እስካልሆንኩለት ድረስ እምነታችሁ አልተሟላም።" ቡኻሪይ ዘግበውታል።

ምእመናንን መውደድ፤ ለራስህ የምትወደው መልካም ነገርንም ለነርሱም ልትወድላቸው ይገባል።

ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ማናችሁም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ እምነቱ አልተሟላም።" ቡኻሪይ ዘግበውታል።