መልስ - ይህ ማለት ትክክለኛ እና መልካም በሆነ ነገር ሰዎች በመካከላቸው መተጋገዛቸው ነው።
የትብብር (መረዳዳት) መገለጫዎች፦
o መብቶችን ወደ ባለቤታቸው ለመመለስ መተባበር፤
o ጨቋኝን በማቀብ ላይ መተባበር፤
o የሰዎችንም የችግረኞችንም ጉዳይ በማሳካት ላይ መተባበር፤
o በበጎ ነገር ሁሉ መተባበር፤
o በሃጢያት፣ በጥቃት እና በጠላትነት ላይ አለመተባበር ናቸው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ። ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ። አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። 2} [ሱረቱል ማኢዳህ፡ 2] ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ማንኛውም ሙእሚን ከሌላ አማኝ ጋር ያለው ግንኙነት እንደ ህንጻ (ጡቦች) ነው፤ አንዱ ሌላኛውን ያጠናክራል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ነብዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ ነው። በመሆኑም አያታልለው፣ አይዋሸው፣ ለጠላት አሳልፎ አይስጠው። የሙስሊምን ጉዳይ ለፈፀመ አላህ ጉዳዩን ይፈፅምለታል፤ የወንድሙን ችግር ላስወገደ አላህ በትንሣኤ ቀን ከችግሮቹ አንዱን ያነሳለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸፈነ አላህ በትንሣኤ ቀን ነውሩን ይሸፍንለታል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።