ጥ 8፡ ህመምን እና ታካሚዎች መጎብኘትን የተመለከቱ ሥነ ምግባሮችን (አዳቦች) ይጥቀሱ?

መልስ-1- ህመም ከተሰማኝ ቀኝ እጄን በሚያመኝ ስፍራ ላይ አድርጌ ሶስት ጊዜ "ቢስሚላህ" ካልኩ በኋላ ሰባት ጊዜ እንዲህ እላለሁ "አዑዙ ቢዒዘቲላሂ ወቁድረቲሂ ሚን ሸሪ ማ አጂዱ ወኡሓዚሩ" (ትርጉሙም: ከማገኘው ክፋት በአላህ ክብር እና ሀይል እጠበቃለሁ እና እጠነቀቃለሁ።"

2- አላህ በወሰነው ነገር ወድጄ እታገሳለሁ፤

3- የታመመ ወንድሜን ለመጠየቅ እሯሯጣለሁ ዱዓእም አደርግለታለሁ፤ እርሱ ዘንድ ግን አብዝቼ አልቀመጥም።

4- ገና ሳይጠይቀኝ ሩቃ አደርግለታለሁ፤

5- በሚችለው መጠን እንዲታገስ፣ ዱዓእ እንዲያደርግ፣ ሶላቱንም እንዲሰግድና በቻለው ልክ ንፅህናውንም እንዲጠብቅ እመክረዋለሁ፤

6- ለህመምተኛ የሚደረገው ዱዓእ ሰባት ጊዜ እንዲህ ማለት ነው፡- "አስአሉ አላሀ አልዐዚም ረበ አልዐርሺል አልዐዚም አን የሽፊየከ" (ትርጉሙም: ታላቅ የሆነውን እና የዐርሽ ጌታ የሆነውን አላህ እንዲያሽርህ እለምነዋለሁ።"