ጥ 3፡ ከወላጆች ጋር ሊኖር የሚገባው ስርአት (አደብ) እንዴት ነው?

መልስ - 1 - አላህን በማመፅ ላይ እስካልሆነ ድረስ ወላጆችን መታዘዝ፤

2- ወላጆችን መኸደም (መንከባከብ)

3 - ወላጆችን ማገዝ፤

4- የወላጆችን ጉዳይ ማሳካት፤

5- ለወላጆች ዱዓእ ማድረግ፤

6- ከእነርሱ ጋር ሲጫወቱ ስርአትን መጠበቅ ይገባል፤ በዚህም መሰረት ከንግግሮች ትንሽ የሆነው “ኡፍ” ማለት እንኳ አይፈቀድም።

7- ለወላጆች የፈገግታ ፊትን ማሳየት ለነርሱ ፊትን አለማጨፍገግ፤

8 - ድምፄን ከወላጆቼ ድምጽ በላይ ከፍ አላደርግም፤ በጥሞና አዳምጣቸዋለሁኝም፤ በንግግራቸው መሀል አላቋረጣቸውምም፤ በስማቸው ነጥየም አልጠራቸውም፤ ይልቁን “አባየ!” “እማየ!” ነው የምላቸው።

9- አባትና እናቴ ክፍል ውስጥ እያሉ ከመግባቴ በፊት ፈቃዳቸውን እጠይቃለሁ፤

10- የወላጆቻችንን እጆችና ግንባራቸውን መሳም።