ጥ 16፡ ወደ ቤት የመግባት እና የመውጣት ሥነ-ስርአትን (አዳብ) ይጥቀሱ?

መልስ- 1- ስወጣም እንዲህ እያልኩ ግራ እግሬን አስቀድሜ ነው፦ "ቢስሚላሂ ተወከልቱ ዐለላሂ ላ ሐውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂ፤ አልላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ አን አዲለ አው ኡዶለ አው አዚለ አው ኡዘለ አው አዝሊመ አው ኡዝለመ አው አጅሀለ አው ዩጅሀለ ዐለይ" (ትርጉሙም፡ በአላህ ስም የምመካውም በእርሱው ነው፤ ብልሀትም ይሁን ሀይል በርሱ ብቻ ነው። አላህ ሆይ! ራሴ ከመሳሳት ወይም ሌሎች እንዲሳሳቱ ከማድረግ፤ ከመንዳለጥ ወይም ሌሎች እንዲንዳለጡ ከማድረግ ከመበደል ወይም ሌሎች እንዲበደሉ ከማድረግ፤ ከመጃጃል ወይም ሌሎች እንዲጃጃሉብኝ ከመሆን በአንተው እጠበቃለሁ።) 2- ስገባም እንዲህ እያልኩ ቀኝ እግሬን አስቀድሜ ነው፡ "ቢስሚላሂ ወለጅና ወቢስሚላሂ ኸረጅና ወዐላ ረቢና ተወከልና" (ትርጉሙም፡ በአላህ ስም ገባን በአላህም ስም ወጣን፤ የምንመካውም በአላህ ነው።)

3- ጥርሴን ሲዋክ በማድርግ እጀምርና ከዚያም ለቤተሰብ አባላቱ ሰላምታ እሰጣለሁ፤