ጥ 12፡ የአመጋገብ ሥነ-ስርአት (አዳብ) እንዴት ነው?

መልስ-

1 - በመብላትና በመጠጣቴ ልዕለ ኃያል የሆነው አላህን መታዘዝን ነው የማስበው፤

2- ከመመገቤ በፊት እጄን እታጠባለሁ፤

3- "ቢስሚላህ" ብየ ከመአዱ መሀልም ከሌላ ሰው ፊትም ሳይሆን በፊትለፊቴ ካለው በቀኝ እጄ እበላለሁ፤

4- "ቢስሚላህ" ማለትን ከረሳሁ ባስታወስኩበት ጊዜ እንዲህ እላለሁ "ቢስሚላሂ አወሊሂ ወአኺሪሂ"

5- ከምግቡ የተገኘውን እመገባለሁ፤ ምግቡንም አላነውርም፤ ከወደድኩት እበላዋለሁ ባልወደ እንኳ አላነውረውም፤

6- ጥቂት ጉርሻዎችን እበላለሁ እንጂ አብዝቼ አልመገብም፤

7- ምግብና መጠጥ ላይ አልተነፍስም፤ እስኪቀዘቅዝ ድረስ ማቆየት ካለብኝ አቆየዋለሁ እንጂ፤

8- ማእዱን ከቤተሰብና ከእንግዳ ጋር እጋራለሁ፤

9- ከእኔ ከሚበልጠኝ ሰው ጋር ስቀርብ ቀድሜው መብላት አልጀምርም፤

10- ስጠጣም "ቢስሚላህ" ብየ ተቀምጬ ሦስት ጊዜ ተጎንጭቼ እጠጣለሁ፤

11- በልቼ ስጨርስም አላህን አመሰግናለሁ።