ጥ10፡ አብሮ የመቀማመጥ ስነ ምግባር (አዳቡ) እንዴት ነው?

መልስ-1- በአብሮነት የተቀማመጡትን ሰዎች ሰላም እላለሁ፤

2 - በአብሮነት ከተቀማመጡት ሰዎች ጫፍ ላይ ባገኘሁት ክፍት ቦታ እቀመጣለሁ፤ ማንንም ከተቀመጠበት አላስነሳም፤ በሁለት ሰዎች መካከል የምቀመጠውም ከፈቀዱልኝ ብቻ ነው፤

3- አቀማመጤንም ሌላም ሰው ለመቀመጥ እንዲችል አድርጌ አሰፋለሁ፤

4- ተቀማማጮቹን በንግግራቸው መሀል አላቋርጣቸውም፤

5- ከተቀመጡት ሰዎች መካከል መሄድ ካለብኝም ከመሄዴ በፊት አስፈቅዳቸዋለሁ፤

6- አብሮ የመቀማመጣችን ጊዜው ካለቀም (የሚከተለውን) የመቀማመጥ ከፋራ ዱዓእ አደርጋለሁ: "ሱብሓነከሏሁመ ወቢሓምዲከ አሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢላ አንተ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይክ" (ትርጉሙም: ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፤ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለም እመሰክራ ለሁ፤ መሀርታህንም እከጅላለሁ ወደ አንተም ተፀፅቻለሁ።)