ጥ 14፡ “ከአላህ ኪታብ (ከቁርአን) አንዲት እንኳ ሐርፍ የቀራ ሰው...” የሚለውን ሐዲሥ ሙላና ከሐዲሡ የምናገኛቸውን የተወሰኑ ጥቅሞቹንም ግለጽ?

መልስ - ከዐብደላህ ቢን መስዑድ በተላለፈ ሐዲሥ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “ከአላህ ኪታብ (ከቁርአን) አንዲት እንኳ ሐርፍ (ሆሄ) የቀራ ሰው በእርሷ ሐሰና (መልካምነት) ይመዘገብለታል። አንድ ሐሰና (መልካምነት) ደግሞ በአስር እጥፍ ነው የሚመነዳው። ይህን ስላችሁ 'አሊፍ ላም-ሚም' አንድ ሐርፍ ነው እያልኳችሁ አይደለም። 'አሊፍ' ራሱን የቻለ ሐርፍ ነው። 'ላም' ራሱን የቻለ ሐርፍ ነው። 'ሚም' ራሱን የቻለ ሐርፍ ነው።" ቲርሚዚይ ዘግበውታል።

ከሐዲሡ ከሚወሰዱ ቁምነገሮች መካከል፡

1- ቁርኣንን መቅራት ያለው ትሩፋት፤

2- በሚቀራው እያንዳንዱ ሐርፍ ሐሰና የሚመዘገብ ስለመሆኑ።