ጥ 15፡ ሱረቱል ኢኽላስን ቅራ እና ተፍሲሯንም አስቀምጥ?

መልስ - ሱረቱል ኢኽላስ እና ተፍሲሯ፦

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

{በል «እርሱ አላህ አንድ ነው። 1 * አሏህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። 2 * አልወለደም፤ አልተወለደምም። 3 * ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።» 4} [ሱረቱል ኢኽላስ፡ 1-4]

ተፍሲር፡

1- {በል «እርሱ አላህ አንድ ነው። 1} የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እንዲህ በላቸው፡- እርሱ አላህ ነው፤ ከእርሱ በቀርም ሌላ አምላክ የለም።

2- {«አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። 2} ማለትም፡- የፍጥረታት ሁሉ ፍላጎት ወደ እርሱ ነው።

3- {«አልወለደም፤ አልተወለደምም። 3} ጥራት ይገባውና ለእርሱ ልጅም ወላጅም የለውም።

4- {«ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።» 4} ከፍጡራኑም ለርሱ ምንም አምሳያ የለውም።