ጥ 5፡ የውዱእ ግዴታዎች ምን ምን ናቸው? ቁጥራቸውስ ስንት ነው?

መልስ - እነዚህ የትኛውም ሙስሊም ውዱእ ሲያደርግ አንዱንም ቢተው ያደረገው ውዱእ ትክክል የማይሆነለት ነው።

1- ፊትን መታጠብ መጉመጥመጥ እና አፍንጫን ጨምሮ ማጠብ ፤

2- እጅን እስከ ክርኖች ማጠብ፤

3- ጆሮን ጨምሮ ጭንቅላትን ማበስ፤

4- እግርን እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ማጠብ፤

5- በውዱእ አካላት መካከል ያለውን ቅደም ተከተል መጠበቅ: ማለትም ፊትን ማጠብ፤ ከዚያም እጆችን ማጠብ፤ ከዚያም ጭንቅላትን ማበስና ከዚያም እግሮችን ማጠብ ነው።

6- ማከታተል፡- ማለትም ውዱእ ሲያደርጉ ከአንደኛው የውዱእ አካል ወደ ሌላኛው ሲሸጋገሩ አካላቱ እስኪደርቅ ድረስ ሳይዘገዩ ማከታተል ነው።

- ማለትም ግማሹን የዉዱእ አካላት አዳርሰው ዘግይቶ ከቆይታ በኋላ ወደሌላኛው አካል መሸጋገሩ ዉዱኡ ትክክለኛ እንዳይሆን ያደርገዋል።