መልስ - እጆችን ሶስት ጊዜ ማጠብ።
ሶስት ጊዜ መግመጥሞጥ እና ውኋ ወደ አፍንጫ ውስጥ ሳብ አድርጎ አፍንጫን አጥርቶ ውኋውን ወደ ውጭ መመለስ።
አፍን መግመጥሞጥ፡- ውሃን በአፍ ውስጥ አስገብቶ ውኋውን ማማታትና ከዚያም መትፋት ነው።
"ኢስቲንሻቅ" ሲባል: ውሃውን በቀኝ እጅ ይዞ በአየር ወደ አፍንጫው ውስጥ መሳብ ነው።
"ኢስቲንሣር" ሲባል ደግሞ: "ኢስቲንሻቅ" ሲያደርጉ ወደ አፍንጫ የሳቡትን ውኋ በግራ እጅ ወደ ውጭ ማስወጣት ነው።
ከዚያም ፊትን ሦስት ጊዜ ማጠብ
ከዚያም እጆችን እስከ ክርኖች ድረስ ሶስት ጊዜ ማጠብ
ከዚያም ጭንቅላትን ማበስ፤ በሁለቱ እጆች ከግንባር ተነስቶ ወደ ማጅራት አብሶ ወደ ግንባር በመመለስ ካበሱ በኋላ ጆሮዎችን ማበስ ነው።
ከዚያም እግርን እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ሶስት ጊዜ ማጠብ
ይህ የተሟላ የሆነው የውዱእ አደራረግ ሲሆን ይህም ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ዑሥማን፣ ዐብዱላህ ቢን ዘይድ እና ሌሎችም ያስተላለፉ እንዲሁም በቡኻሪይ እና ሙስሊም የተዘገበ ሐዲሥ ላይ የተገለጸ ነው። እንዲሁም በቡኻሪይ እና በሌሎችም ዘገባዎች እንዲህ መባሉ ተረጋግጧል፡- “አንድ አንድ ጊዜም ውዱእ አድርገዋል፤ ሁለት ሁለት ጊዜም ውዱእ አድርገዋል።” ማለትም፡ እያንዳንዱን የውዱእ ክፍል አንድ አንድ ጊዜም ሁለት ሁለት ጊዜም እያጠቡ ውዱእ ያደርጉ ነበር ነው።