ጥ 6 - ሶላትን ካጠናቀቅክ በኋላ የሚባለው ዚክር ምንድን ነው?

መልስ - ሶስት ጊዜ "አስተግፊሩሏህ" ካለ በኋላ

- "አሏሁምመ አንተስ-ሰላም ወሚንከስ-ሰላም ተባረክተ ያ ዘል-ጀላሊ ወል-ኢክራም" (ትርጉሙም፡

አላህ ሆይ! አንተ "አስ-ሰላም" ነህ። ሰላምም ከአንተው ነው የሚመጣው። የግርማና የልቅና ባለቤት የሆንከው ጌታየ ሆይ ክብርህ ይስፋ።)

- "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፡ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር አሏሁመ ላ ማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መናዕተ ወላ የንፈዑ ዘል-ጀዲ ሚንከል-ጀድ"

(ትርጉሙም፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም፤ ተጋሪ የለውም። ንግሥናም ምስጋናም የእርሱ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! አንተ የሰጠኸውን የሚያቅበው የለም። የከለከልከውንም ማንም ሊሰጥ አይችልም። እድለኝነትም ሊጠቅም አይችልም። እድለኝነትም ካንተው ነው።)

- "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፡ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ላ ሓውላ ወላ ቁወተን ኢላ ቢላህ ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወላ ነዕቡዱ ኢላ ኢያህ ለሁን-ኒዕመቱ ወለሁል-ፈድሉ ወለሁሥ-ሠናኡል ሐሰን ላ ኢላሀ ኢለላህ ሙኽሊሲነ ለሁድ-ዲን ወለው ከሪሀል-ካፊሩን"

(ትርጉሙም፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም፤ ተጋሪ የለውም። ንግሥናም ምስጋናም የእርሱ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። ከአላህ በስተቀር ምንም ሃይልም ብልሀትም የለም። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ከርሱም ሌላ አንገዛም። ችሮታው የርሱ ብቻ ነው። ውዳሴም ለእርሱ ብቻ ነው። ከአላህ በስተቀር ሌላ በእውነት አምልኮ የሚገባ አምላክ የለም። ከሓዲዎች ቢጠሉም (እኛ) ሃይማኖታችንን በኢኽላስ ለርሱ ያጠራን ነን።)

- "ሱብሐነላህ" (ትርጉሙም፡ አላህ ጥራት ይገባው) ሰላሳ ሶስት ጊዜ፤

- "አልሐምዱሊህ" (ትርጉሙም፡ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው) ሰላሳ ሶስት ጊዜ፤

- "አላሁ አክበር" (ትርጉሙም፡ አላህ የላቀ ነው) ሰላሳ ሶስት ጊዜ፤

ከዚያም እንዲህ ብሎ መቶ ይሞላል፦ - "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፡ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር"

(ትርጉሙም፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም፤ ተጋሪ የለውም። ንግሥናም ምስጋናም የእርሱ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።)

- ሱረቱ አል-ኢኽላስን እና ሱረቱል ፈለቅን ("ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ") እና ሱረቱ-ን-ናስን (“ቁል አዑዙ ቢረቢ-ን-ናስ”) ከፈጅርና ከመግሪብ ሰላት በኋላ ሶስት ሶስት ጊዜ ከሌሎቹ ሶላቶች በኋላ ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ መቅራት፤

አየተል ኩርሲይን አንድ ግዜ መቅራት፤