ጥ 23፡ የሶላት ሱናዎች ምን ምን ናቸው?

መልስ- እንደሚከተለው አስራ አንድ ናቸው፦

1 - ከተክቢረተል ኢሕራም በኋላ እንዲህ ማለት: የመክፈቻውን ዱዓእ (ዱዓኡል ኢስቲፍታሕ) እንዲህ ማለት፡- «ሱብሓነከሏሁም ወቢሓምዲከ ወተባረከ ኢስሙከ ወተዓላ ጀዱከ ወላኢላሀ ገይሩክ» [ትርጉሙም ጥራትና ልቅና ለአንተ ይሁን አምላኬ ሆይ ምስጋናም ለአንተ ይሁን፤ ስምህም የላቀ ነው፤ ግርማህም ከፍ ከፍ ይበል፤ ካንተ በቀርም አምላክ የለም። ማለት ነው]

2 - «አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧኒ ረጂም» ማለት፤

3 - ቢስሚላህ፤

4 - አሚን ማለት፤

5- ከአል-ፋቲሐ በኋላ ተጨማሪ ሱራን መቅራት፤

6- የኢማሙ ጮክ ብሎ መቅራት፤

7- ከምስጋናው (ሰሚዐሏሁ ሊመን ሓሚደህ ካሉ) በኋላ እንዲህ ማለት፡- ”ሚልኡ ሰማዋቲ ወሚልኡል አርዲ ወሚልኡ ማሺእተ ሚን ሸይኢን ባዕዱ“ ትርጉሙም: "ምስጋና በሰማያት ሙሉ በምድር ሙሉ ላንተ ይሁን፤ ከዚያም በኋላ በወደደህ ነገር ሙሉም ምስጋና ላንተ ይሁን።"

8- በሩኩዕ ጊዜ ከሚደረገው ተስቢሕ ወይንም ሁለተኛውና ሦስተኛው ተስቢሕ ከዚያም በላይ መጨመር

9- በሱጁድ ጊዜ ከአንድ ጊዜ በላይ የሚደረገው ተስቢሕ፤

10 - በሱጁዶች መካከል ከአንድ ጊዜ በላይ “ረቢ-ግ-ፊርሊ” ማለት:

11 - በመጨረሻው ተሸሁድ በሳቸውም በቤተሰቦቻቸውም የአላህ ሰላት እና ሰላም እንዲሁም በረካ እንዲሰፍን ከተማፀነ በኋላ ያሻውን ዱዓእ ያድርግ።

አራተኛ፡ ድርጊታዊ የሚባሉ ሱና የሆኑ ድርጊቶች፡-

1- ተክቢረተል ኢሕራም እያደረጉ እጆችን ወደ ላይ ማንሳት፤

2 - በሩኩዕም ጊዜ (እጆችን ማንሳት)

3 - ከሩኩዕ ቀና ሲሉም (እጆችን ማንሳት)

4- ከዚያም በኋላ እጆችን አስተካክሎ ማስቀመጥ፤

5- የቀኝ እጅን በግራ እጅ ላይ ደርቦ ማስቀመጥ፤

6- ሱጁድ ወደሚያደርጉበት ቦታ መመልከት፤

7- ሲቆም በእግሮች መካከል ከፈት አድርጎ መቆም፤

8- የሁለቱ እጆች ጣቶችን ፈታ አድርጎ ጉልበትን በመያዝ፤ ጀርባን ቀጥ በማድረግ ጭንቅላትንም በጀርባ ትይዩ አድርጎ ሩኩዕ ማድረግ(መጎንበስ)

9- የሱጁድ አካላትን በመሬት ላይ አመቻችቶ እያንዳንዱ ክፍል መሬት እንዲነካ በማድረግ ሱጁድ መውረድ፤

10 - አካላትን ማራራቅ: እጆችን ከጎድን፣ ሆድን ከጭኖች፣ ጭኖችን ከተረከዞች መለየት፤ እንዲሁም ጉልበቶችን ከፈት ማድረግ፤ ተረከዞችን ቀጥ አድርጎ መትከል፤ የእግር ጣቶችን ውስጠኛው ክፍል ለያይቶ መሬት ላይ ማድረግ፤ ሁለት እጆችን ጣቶቻቸውን ገጥሞ በመዘርጋት በትከሻ ትይዩ ማድረግ፤

11- በሁለቱ ሱጁዶች መካከል እና ለመጀመሪያው ተሸሁድ ሲቀመጡ "ኢፍቲራሽ" አድርጎ መቀመጥ እና በሁለተኛው ተሸሁድ ደግሞ "ተወሩክ" በሚባለው አቀማመጥ መቀመጥ፤

12- በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሲቀመጡ እጆችን ጣቶቻቸውን ገጥሞ በመዘርጋት ጭን ላይ ማድረግ ነው። ምናልባት ትንሿን ጣት እና ቀለበት ጣትን ጨብጦ የመሀል ጣትን ከአውራ ጣት ጋር አብሮ ክብ እንዲሰሩ ማድረግ፤ በተሸሁድም አቀማመጡ እንዲሁ ነው።

13- አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ በሚልበት ጊዜ ወደቀኝና ወደ ግራ መዞር፦