መልስ - ትርጉሙ፡- አላህ እሳቸውን አብሳሪና አስፈራሪ አድርጎ ለዓለማት የላካቸው መልዕክተኛው መሆናቸውን መመስከር ማለት ነው።
በዚህ ያመነ የሚከተሉት ነገሮች ግዴታ ይሆኑበታል፦
1- ያዘዙትን መታዘዝ፤
2- የተናገሩትን አምኖ መቀበል፤
3- እርሳቸውን አለማመፅ፤
4- እሳቸው በደነገጉት ካልሆነ በቀር አላህ አለማምለክ ነው። ይኸውም ሱናቸውን በመከተል እና ቢድዓን በመተው ነው።
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ።} (ሱረቱ-አንኒሳእ፡ 80) ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፦ {ከልብ ወለድም አይናገርም። እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም። 4} [ሱረቱ-ነጅም 3፡4] ልዕለ ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ።21} [ሱረቱል አሕዛብ፡ 21]