መልስ- አላህ፡- ትርጉሙም ተጋሪ የሌለው ብቸኛው በእውነት የሚመለክ አምላክ ማለት ነው።
አር-ረብ፡- ትርጉሙም ጥራት የተገባው አምላካችን አላህ ብቸኛው የሁሉም ፈጣሪ፣ ባለቤት፣ ሰጪና አስተናባሪው ማለት ነው።
አስ-ሰሚዕ፡- የመስማት ችሎታው ሁሉንም ነገር የሚያካልል እና በዓይነትም በብዛት የተለያዩ የሆኑ ድምፆችን በሙሉ የሚሰማ ማለት ነው።
አል-በሲር፡ ሁሉንም ነገር የሚያይ እና ትንሹም ይሁን ትልቁን ሁሉ የሚመለከት ነው።
አል-ዓሊም፡ እውቀቱ ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱን ሁሉ ያካለለ ነው።
አር-ረሕማን፡ እዝነቱ ለእያንዳንዱ ህያው ፍጡር ሁሉ የተዘረጋ ሲሆን ፍጡራን ሁሉ በእዝነቱ ስር ናቸው።
አር-ረዛቅ፡- የሰውም፣ የጂንም እና የተንቀሳቃሽ ህያው ሁሉ ሲሳይ እርሱ ዘንድ የሆነ ነው።
አል-ሓይ፡- የማይሞት ህያው የሆነ ነው። ፍጥረታት ሁሉ ሟች ናቸው።
አል-ዓዚም፡ በስሙም በባህሪያቱም እንዲሁም በድርጊቶቹም ፍጹምነት እና ልዕልና ያለው ነው።