ጥ 31፡ አላህን መፍራት ምንድን ነው? አላህ ላይ ተስፋ ማድረግ ሲባልስ ምንድን ነው? ማስረጃውስ?

መልስ- አላህን መፍራት ሲባል፡- አላህን እና ቅጣቱን መፍራት ነው።

ተስፋን አላህ ላይ ማድረግ ሲባል ደግሞ፡ የአላህን ምንዳ፣ ይቅር ባይነት እና ምሕረትን ተስፋ ማድረግ ነው።

ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {እነዚያ እነርሱ የሚግገዟቸው ማንኛቸውም (ወደ አላህ) በጣም ቀራቢያቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን (ሥራ) ይፈልጋሉ። እዝነቱንም ይከጅላሉ። ቅጣቱንም ይፈራሉ። የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና።} [ሱረቱል ኢስራእ፡ 57] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው። 49 ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መሆኑን (ንገራቸው)። 50} [ሱረቱል ሒጅር፡ 49-50]