ጥ 15፡ የእምነትን ምሰሶዎችን አብራራ?

መልስ - በላቀው አላህ ማመን፡

§ አንተን የፈጠረህ፣ ሲሳይም የሚለግስህ፣ የፍጡራን ሁሉ ባለቤትና ገዥ አላህ መሆኑን ልታምን ነው።

§ በእውነት የሚመለከው እርሱው ነው፤ ከእርሱም ውጭ በእውነት ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም።

§ እርሱ ታላቅና ምሉዕ የሆነና ምስጋናም ሁሉ የተገባው ነው። ለእርሱም ውብ ስሞችና የላቁ ባህሪያት አሉት። ከፍጡራኑም ምንም ዓይነት ብጤም ሆነ አምሳያ የለውም።

በመላእክቶች ማመን፡

መላዕክት አላህ እርሱን እንዲያመልኩት ከብርሀን የፈጠራቸውና ለትእዛዙ ሙሉ በሙሉ ታዛዥ የሆኑ ፍጥረታት ናቸው።

- ከእነርሱ መካከል ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም የሚባል አለ፤ ለነብያት ራዕይን ይዞ የሚወርድ ነው።

በመጻሕፍቱ ማመን፡

ይህን ስንል አላህ ወደ መልእክተኞቹ ያወረዳቸው መጻሕፍቶችን ማለታችን ነው።

በነብዩ ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ የወረደውን ቁርኣን።

በዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ በወረደው ኢንጅል።

በሙሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ በወረደው ተውራትን።

በዳውድ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ በወረደው ዘቡር።

በኢብራሂም እና በሙሳ ዓለይሂማ ሰላም ላይ በወረደው ሱሑፍ።

በመልዕክተኞች ማመን፡

ማለት እነዚያ ባርያዎቹን እንዲያስተምሩ፣ በመልካም እና በጀነት እንዲያበስሩ፣ ከክፉና ከእሳትም እንዲያስጠነቅቁ አላህ ወደ ፍጡራኑ የላካቸው መልዕክተኞች ናቸው።

ከመካከላቸው በላጮቹ፡- ኡሉ-ል-ዓዝም ሲሆኑ እነሱም፡-

ኑሕ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን

ኢብራሂም የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን

ሙሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን

ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን

ነብዩ ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ናቸው።

በመጨረሻው ቀን ማመን፡

ይሀውም ሰዎች ከሞቱ በኋላ በመቃብር ውስጥ፣ በቂያማ ቀን፣ ከሞት በሚነሱበትና ፍርዳቸውንም በሚያገኙበት ቀን፣ የጀነት ሰዎች በመኖሪያቸው የጀሀነም ሰዎችም በመኖሪያቸው የሚሰፍሩበት ነው።

በቀደር ክፉውም ሆነ ደጉን ማመን፡

ቀደር፡- አላህ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የሚሆነውን ነገር ሁሉ እንደሚያውቅ፤ ያንንም በጥብቁ ሰሌዳ (በለውሐል መሕፉዝ) ላይ እንዳሰፈረው እና መገኘቱም ሆነ መፈጠሩ በእርሱ መሻት የሚከናወን መሆኑን ማመን ነው።

የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው።} [ሱረቱል ቀመር 49]

አራት እርከኖች አሉት፦

የመጀመርያው እርከን፡ ጥራት የተገባው አላህ የሆነውንም የሚሆነውንም ሁሉ አስቀድሞ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑ

ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው። ዝናብንም ያወርዳል። በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል። ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም። ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም። አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው። 34} [ሉቅማን፡ 34]

ሁለተኛው እርከን፡- አስቀድሞ የወሰነውንና የፈረደውን ሁሉ በለውሐል መሕፉዝ የመዘገበው መሆኑን ማመን ነው። በመሆኑም የተከሰተውም ይሁን የሚከሰተውም ሁሉ እርሱ ዘንድ ባለው መጽሐፍ ሰፍሯል።

ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው። ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም። በየብስና በባሕር ያለውንም ሁሉ ያውቃል። ከቅጠልም አንዲትም አትረግፍም የሚያውቃት ቢሆን እንጅ። ከቅንጣትም በመሬት ጨለማዎች ውስጥ የለም ከእርጥብም ከደረቅም አንድም የለም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውሰጥ (የተመዘገበ) ቢሆን እንጅ። 59} [ሱረቱል አል-አንዓም 59]

ሦስተኛው እርከን፡ ነገራቶችን ሁሉ እውን የሚሆኑት በእርሱ መሻት ነው። በመሆኑም በእርሱ ፈቃድ ካልሆነ በቀር ከእርሱም ሆነ ከፍጥረቱ የሚከሰት ምንም ዓይነት ነገር የለም።

ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {ከናንተ ቀጥተኛ መሆንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)። 28 የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም። 29} [ሱረቱ-አትተክዊር፡28-29]

አራተኛው እርከን፡- ነገራቶችን ሁሉ የፈጠረው እርሱ መሆኑን ማመን ነው። ራሳቸውን፣ ባህሪያቸው፣ እንቅስቃሴዎቻቸውና በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ የፈጠረው እርሱ ነው።

ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲሆን።» 96} [ሱረቱ-አስሷፍፋት 96]