ጥ 10፡ የተውሒድ ዓይነቶች ስንት ናቸው?

መልስ-1- ተውሒድ አር-ሩቡቢያህ (የጌትነት አሀዳዊነቱ)፡- አላህ ብቸኛው የሁሉም ፈጣሪ፣ ለጋሽ፣ ባለቤትና ተቆጣጣሪ መሆኑን ማመን ነው።

2- ተውሒድ አል-ኡሉሂያ (የአምልኮ አሀዳዊነቱ)፡- በአምልኮ አላህን ብቻ ነጥሎ ማምለክ ነው። ከላቀው አላህ በስተቀር ማንም በሐቅ የሚመለክ የለም።

3- ተውሒዱል አስማእ ወስሲፋት (በስምና ባህርያቱ ያለው አሀዳዊነት)፡- በቁርአንና በሐዲሥ በተጠቀሱት የአላህ ስም እና ባህሪያቱ ያለ ምንም ምሳሌ መስጠት፣ ከፍጡራንም ጋ ሳያመሳስሉ እና ውድቅም ሳያደርጉ በቁርኣን እና ሱንና በተጠቀሰው መልኩ አምኖ መቀበል ነው።

ለሶስቱ የተውሒድ ዓይነቶች ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {(እርሱ) የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው። እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ። ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን? 65} [ሱረቱ መርየም፡ 65]